54. ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ።
55. በጥልቁ ጒድጓድ ውስጥ ሳለሁ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተን ስም ጠራሁ።
56. ልመናዬን ሰምተሃል፤ “ርዳታም ፈልጌ ስጮኽ፣ከመስማት ጆሮህን አትከልክል።”
57. በጠራሁህ ጊዜ ቀረብኸኝ፣እንዲሁም፣ “አትፍራ” አልኸኝ።
58. ጌታ ሆይ፤ ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤ሕይወቴንም ተቤዠህ።
59. እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኔ ላይ የተደረገውን ግፍ አየህ፤ፍርዴን ፍረድልኝ!