31. እግዚአብሔር ለእናንተ ምሕረት ከማድረጉ የተነሣ፣ እነርሱም ምሕረት ያገኙ ዘንድ አሁን የማይታዘዙ ልጆች ሆነዋል፤
32. እግዚአብሔር ለሁሉም ምሕረት ያደርግ ዘንድ ሰውን ሁሉ ባለመታዘዝ ዘግቶታልና።
33. የእግዚአብሔር የጥበቡና የዕውቀቱ ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው!ፍርዱ አይመረመርም፤ለመንገዱም ፈለግ የለው …
34. “የጌታን ልብ ያወቀ ማነው?አማካሪውስ የነበረ ማን ነው?”
35. “እግዚአብሔር መልሶ እንዲሰጠው፣ለእግዚአብሔር ያበደረ ከቶ ማን ነው?”
36. ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።