ራእይ 4:9-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ሕያዋን ፍጡራኑ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ክብር፣ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፣

10. ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ተደፍተው፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ይሰግዱ ነበር፤ አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው እንዲህ ይላሉ፤

11. “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤ክብርና ሞገስ፣ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፤በፈቃድህም ተፈጥረዋልና፤ሆነዋልምና።”

ራእይ 4