ራእይ 16:6-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ፣አንተም ደግሞ ደም እንዲጠጡ አደረግሃቸው፤ ይህ የሚገባቸው ነውና።”

7. እንዲሁም ከመሠዊያው እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤“አዎን፤ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤ፍርድህ እውነትና ጽድቅ ነው።”

8. አራተኛውም መልአክ ጽዋውን በፀሓይ ላይ አፈሰሰ፤ ፀሓይም ሰዎችን በእሳት እንድታቃጥል ኀይል ተሰጣት።

ራእይ 16