3. ተጣጠቢ፤ ሽቶ ተቀቢ፤ እንዲሁም የክት ልብስሽን ልበሺ፤ ከዚያም ወደ ዐውድማው ውረጂ፤ ይሁን እንጂ በልቶና ጠጥቶ እስኪያበቃ ድረስ፣ እዚያ መሆንሽን እንዳያውቅ ይሁን።
4. በተኛም ጊዜ፣ የሚተኛበትን ቦታ ልብ ብለሽ እዪና ሄደሽ እግሩን ገልጠሽ ተኚ፤ ከዚያም የምታደርጊውን ራሱ ይነግርሻል።”
5. ሩትም፣ “ያልሽውን ሁሉ አደርጋለሁ” አለቻት።
6. ስለዚህ ተነሥታ ወደ ዐውድማው ወረደች፤ አማቷ አድርጊ ያለቻትንም ሁሉ አደረገች።