1. ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አቆመች፤
2. ፍሪዳዋን አረደች፤ የወይን ጠጇን ጠመቀች፤ማእዷንም አዘጋጀች።
3. ሴት አገልጋዮቿንም ላከች፤ከከተማዪቱም ከፍተኛ ቦታ ተጣራች።
4. እርሷም ማመዛዘን ለጐደላቸው፣“ማስተዋል የሌላችሁ ሁሉ ወደዚህ ኑ” አለች።
5. “ኑ፤ ምግቤን ተመገቡ፤የጠመቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።
6. የሞኝነት መንገዳችሁን ተዉ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤በማስተዋልም መንገድ ተመላለሱ።
7. “ፌዘኛን የሚገሥጽ ሁሉ ስድብን በራሱ ላይ ያመጣል፤ክፉውን ሰው የሚዘልፍ ሁሉ ውርደት ያገኘዋል።