ምሳሌ 7:10-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ከዚያም አንዲት ሴት ልታገኘው ወጣች፤እንደ ዝሙት አዳሪ ለብሳ፣ ለማሳሳት ታጥቃ።

11. ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤እግሮቿ አርፈው ቤት አይቀመጡም፤

12. አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ፤በየማእዘኑም ታደባለች።

13. አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ኀፍረቷንም ጥላ እንዲህ አለችው፤

14. “በቤቴ የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ፤

15. ስለዚህ አንተን ለማግኘት ወጣሁ፤ፈልጌህ ነበር፤ ይኸው አገኘሁህ።

16. ዐልጋዬን ከግብፅ የመጣ፣ጌጠኛ በፍታ አልብሼዋለሁ።

17. ዐልጋዬን፣የከርቤ፣ የዓልሙንና የቀረፋ ሽቱ አርከፍክፌበታለሁ።

ምሳሌ 7