ምሳሌ 6:30-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. ሌባ በተራበ ጊዜ ራቡን ለማስታገሥ ቢሰርቅ፣ሰዎች አይንቁትም።

31. በቤቱ ያለውን ሀብት ሁሉ የሚጠይቀው ቢሆንም፣ከተያዘ ሰባት ዕጥፍ መክፈል አለበት።

32. የሚያመነዝር ሰው ግን ማመዛዘን ይጐድለዋል፤እንዲህ የሚያደርግ ሁሉ ራሱን ያጠፋል።

33. መደብደብና ውርደት ዕጣው ነው፤ኀፍረቱም ከቶ አይወገድም፤

34. ቅናት የባልን ቊጣ ይቀሰቅሳልና፤በሚበቀልበትም ጊዜ ምሕረት አያደርግም።

35. ምንም ዐይነት ካሣ አይቀበልም፤የቱንም ያህል ብዙ ቢሆን መማለጃን እሺ አይልም።

ምሳሌ 6