ምሳሌ 6:24-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. እርሷም ከምግባረ ብልሹ ሴት፣ልዝብ አንደበት ካላት ዘልዛላ ሴት ትጠብቅሃለች።

25. ውበቷን በልብህ አትመኝ፤በዐይኗም አትጠመድ፤

26. ጋለሞታ ሴት ቊራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች።

27. ለመሆኑ ልብሱ ሳይቃጠል፣በጒያው እሳት መያዝ የሚችል ሰው አለን?

28. አንድ ሰው እግሮቹ ሳይቃጠሉ፣በፍም ላይ መሄድ ይችላልን?

29. ከሰው ሚስት ጋር የሚተኛም እንደዚሁ ነው፤የሚደርስባትም ከቅጣት አያመልጥም።

30. ሌባ በተራበ ጊዜ ራቡን ለማስታገሥ ቢሰርቅ፣ሰዎች አይንቁትም።

31. በቤቱ ያለውን ሀብት ሁሉ የሚጠይቀው ቢሆንም፣ከተያዘ ሰባት ዕጥፍ መክፈል አለበት።

ምሳሌ 6