ምሳሌ 6:16-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፦

17. ትዕቢተኛ ዐይን፣ሐሰተኛ ምላስ፣ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች፣

18. ክፋትን የሚያውጠነጥን ልብ፣ወደ ክፋት የሚቻኰሉ እግሮች፣

19. በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።

20. ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ትእዛዝ አክብር፤የእናትህንም ትምህርት አትተው።

21. ምንጊዜም በልብህ አኑራቸው፤በዐንገትህም ዙሪያ እሰራቸው።

22. በምትሄድበት ሁሉ ይመሩሃል፤በምትተኛበት ጊዜ ይጠብቁሃል፤በምትነቃበት ጊዜም ያነጋግሩሃል።

23. እነዚህ ትእዛዞች መብራት ናቸውና፤ይህችም ትምህርት ብርሃን፣የተግሣጽ ዕርምትም የሕይወት መንገድ ናት፤

24. እርሷም ከምግባረ ብልሹ ሴት፣ልዝብ አንደበት ካላት ዘልዛላ ሴት ትጠብቅሃለች።

25. ውበቷን በልብህ አትመኝ፤በዐይኗም አትጠመድ፤

26. ጋለሞታ ሴት ቊራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች።

27. ለመሆኑ ልብሱ ሳይቃጠል፣በጒያው እሳት መያዝ የሚችል ሰው አለን?

ምሳሌ 6