ምሳሌ 6:16-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፦

17. ትዕቢተኛ ዐይን፣ሐሰተኛ ምላስ፣ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች፣

18. ክፋትን የሚያውጠነጥን ልብ፣ወደ ክፋት የሚቻኰሉ እግሮች፣

19. በውሸት ላይ ውሸት የሚጨምር ሐሰተኛ ምስክር፣በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚጭር ሰው።

ምሳሌ 6