ምሳሌ 6:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ልጄ ሆይ፤ ለጎረቤትህ ዋስ ብትሆን፣ስለ ሌላውም ሰው እጅ መትተህ ቃል ብትገባ፣

2. በተናገርኸው ነገር ብትጠመድ፣ከአፍህ በወጣውም ቃል ብትያዝ፣

3. ልጄ ሆይ፤ ራስህን ለማዳን ይህን አድርግ፤በጎረቤትህ እጅ ስለ ወደቅህ፣ሄደህ ራስህን አዋርድ፤ጎረቤትህን አጥብቀህ ነዝንዘው።

4. ዐይኖችህ እንቅልፍ አይያዛቸው፣ሽፋሽፍቶችህም አያንጐላጁ።

ምሳሌ 6