ምሳሌ 5:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. በዕድሜህ መጨረሻ ታቃሥታለህ፤ሥጋህና ሰውነትህ ሲከዳህ።

12. እንዲህም ትላለህ፤ “ምነው! ተግሣጽን ጠላሁ፤ልቤስ ምነው! መታረምን ናቀ፤

13. የመምህሮቼን ቃል አልሰማሁም፤አሰልጣኞቼንም አላደመጥኋቸውም፤

14. በመላው ጉባኤ ፊት፣ወደ ፍጹም ጥፋት ተቃርቤአለሁ።”

15. ከገዛ ማጠራቀሚያህ ውሃ፣ከገዛ ጒድጓድህም የሚፈልቀውን ውሃ ጠጣ።

ምሳሌ 5