8. “ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት።
9. ተናገር፤ በቅንነትም ፍረድ፤የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”
10. ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል?ከቀይ ዕንቊ እጅግ ትበልጣለች።
11. ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤የሚጐድልበትም ነገር የለም።
12. በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም።
13. የበግ ጠጒርና የተልባ እግር መርጣ፣ሥራ በሚወዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች።
14. እንደ ንግድ መርከብ፣ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች።
15. ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች።
16. ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች።
17. ብርታትን ታጥቃ ሥራዋን ታከናውናለች፤ክንዶቿም ለሥራ ብርቱ ናቸው።
18. ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም።