ምሳሌ 31:21-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና።

22. ለመኝታዋ የዐልጋ ልብስ ትሠራለች፤ቀጭን በፍታና ሐምራዊ ልብስ ለብሳለች።

23. ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከልበአደባባይ በተቀመጠ ጊዜ የተከበረ ነው።

24. የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች።

25. ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤መጭውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች።

26. በጥበብ ትናገራለች፤በአንደበቷም ቀና ምክር አለ።

27. የቤተ ሰዎቿን ጒዳይ በትጋት ትከታተላለች፤የስንፍና እንጀራ አትበላም።

28. ልጆቿ ተነሥተው፤ ቡርክት ይሏታል፤ባሏም እንዲሁ፤ ሲያመሰግናትም እንዲህ ይላል፤

29. “ብዙ ሴቶች መልካም አድርገዋል፤አንቺ ግን ሁሉንም ትበልጫለሽ።”

30. ቊንጅና አታላይ ነው፤ ውበትም ይረግፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን የተመሰገነች ናት።

31. የሚገባትን ሽልማት ስጧት፤ሥራዋም በየአደባባዩ ያስመስግናት።

ምሳሌ 31