ምሳሌ 31:17-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ብርታትን ታጥቃ ሥራዋን ታከናውናለች፤ክንዶቿም ለሥራ ብርቱ ናቸው።

18. ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም።

19. በእጇ እንዝርት ትይዛለች፤በጣቶቿም ዘንጒን ታሾራለች።

20. ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች።

21. በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና።

22. ለመኝታዋ የዐልጋ ልብስ ትሠራለች፤ቀጭን በፍታና ሐምራዊ ልብስ ለብሳለች።

23. ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከልበአደባባይ በተቀመጠ ጊዜ የተከበረ ነው።

24. የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች።

25. ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤መጭውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች።

26. በጥበብ ትናገራለች፤በአንደበቷም ቀና ምክር አለ።

ምሳሌ 31