ምሳሌ 31:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች።

16. ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች።

17. ብርታትን ታጥቃ ሥራዋን ታከናውናለች፤ክንዶቿም ለሥራ ብርቱ ናቸው።

18. ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም።

19. በእጇ እንዝርት ትይዛለች፤በጣቶቿም ዘንጒን ታሾራለች።

20. ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች።

ምሳሌ 31