2. “እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ ጅል ነኝ፤ሰው ያለው ማስተዋል የለኝም።
3. ጥበብን አልተማርሁም፤ስለ ቅዱሱም ዕውቀት የለኝም።
4. ወደ ሰማይ የወጣ፣ የወረደስ ማነው?ነፋስን በእጁ ሰብስቦ የያዘ ማነው?ውሆችንስ በመጐናጸፊያው የጠቀለለ ማነው?የምድርን ዳርቻዎች ሁሉ የወሰነ ማነው?ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል?የምታውቅ ከሆነ እስቲ ንገረኝ!
5. “የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንከን የለበትም፤እርሱ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻቸው ነው።
6. በእርሱ ቃል ላይ አንዳች አትጨምር፤አለዚያ ይዘልፍሃል፤ ሐሰተኛም ያደርግሃል።
7. “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሁለት ነገር እለምንሃለሁ፤እነዚህንም ከመሞቴ በፊት አትከልክለኝ፤
8. ሐሰትንና ሐሰት መናገርን ከእኔ አርቅልኝ፤ድኽነትንም ሆነ ብልጽግናን አትስጠኝ፤ብቻ የዕለት እንጀራዬን ስጠኝ።
9. ያለዚያ ግን ያለ ልክ እጠግብና እክድሃለሁ፤‘እግዚአብሔር ማን ነው?’ እላለሁ፤ወይም ድኻ እሆንና እሰርቃለሁ፤የአምላኬንም ስም አሰድባለሁ።
10. “አገልጋይን በጌታው ፊት በክፉ አታንሣው፤አለዚያ ይረግምህና ጒዳት ያገኝሃል።