ምሳሌ 3:32-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. እግዚአብሔር ጠማማን ሁሉ ይጸየፋልና፤ለቅን ሰው ግን ምስጢሩን ይገልጥለታል።

33. የእግዚአብሔር ርግማን በክፉዎች ቤት ላይ ነው፤የጻድቃንን ቤት ግን ይባርካል።

34. እርሱ በዕቡያን ፌዘኞች ላይ ያፌዛል፤ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል።

35. ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፤ሞኞችን ግን ለውርደት ያጋልጣቸዋል።

ምሳሌ 3