ምሳሌ 3:29-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. አንተን ተማምኖ በአጠገብህ በተቀመጠ፣በጎረቤትህ ላይ ክፉ አትምከርበት።

30. ምንም ጒዳት ሳያደርስብህ፣ያለ ምክንያት ሰውን አትክሰስ።

31. በክፉ ሰው አትቅና፤የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ፤

32. እግዚአብሔር ጠማማን ሁሉ ይጸየፋልና፤ለቅን ሰው ግን ምስጢሩን ይገልጥለታል።

33. የእግዚአብሔር ርግማን በክፉዎች ቤት ላይ ነው፤የጻድቃንን ቤት ግን ይባርካል።

ምሳሌ 3