ምሳሌ 3:23-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ከዚያም መንገድህን በሰላም ትሄዳለህ፤እግርህም አይሰናከልም፤

24. ስትተኛ አትፈራም፤ትተኛለህ እንቅልፍህም ጣፋጭ ይሆናል።

25. ድንገተኛን መከራ፣በክፉዎች ላይ የሚደርሰውንም ጥፋት አትፍራ፤

26. እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፤እግርህንም በወጥመድ ከመያዝ ይጠብቃል።

27. ማድረግ እየቻልህለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ አትቈጠብ።

28. አሁን በእጅህ እያለ፣ጎረቤትህን፣ “ቈይተህ ተመለስ፤ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው።

29. አንተን ተማምኖ በአጠገብህ በተቀመጠ፣በጎረቤትህ ላይ ክፉ አትምከርበት።

ምሳሌ 3