ምሳሌ 3:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል።

3. ፍቅርና ታማኝነት ከቶ አይለዩህ፤በዐንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው።

4. በዚያን ጊዜ ሞገስንና መልካም ስምን፣በእግዚአብሔርና በሰው ዘንድ ታገኛለህ።

5. በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤

6. በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።

ምሳሌ 3