ምሳሌ 3:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤በማስተዋል ሰማያትን በየስፍራቸው አጸና፤

20. በዕውቀቱ ቀላያት ተከፈሉ፤ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ።

21. ልጄ ሆይ፤ ትክክለኛ ፍርድንና አስተውሎ መለየትን ጠብቅ፤እነዚህ ከእይታህ አይራቁ፤

22. ለነፍስህ ሕይወት፣ለዐንገትህም ጌጥ ይሆናሉ።

23. ከዚያም መንገድህን በሰላም ትሄዳለህ፤እግርህም አይሰናከልም፤

ምሳሌ 3