ምሳሌ 3:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. እርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና።

15. ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።

16. በቀኝ እጇ ረጅም ዕድሜ አለ፤በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች።

17. መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ጐዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።

18. ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤የሚይዟትም ይባረካሉ።

ምሳሌ 3