12. አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ ሁሉ፣ እግዚአብሔርም የሚወደውን ይገሥጻልና።
13. ጥበብን የሚያገኛት፣ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርጋት ሰው ቡሩክ ነው፤
14. እርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና።
15. ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።
16. በቀኝ እጇ ረጅም ዕድሜ አለ፤በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች።
17. መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ጐዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።
18. ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤የሚይዟትም ይባረካሉ።
19. እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤በማስተዋል ሰማያትን በየስፍራቸው አጸና፤
20. በዕውቀቱ ቀላያት ተከፈሉ፤ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ።