6. ክፉ ሰው በራሱ ኀጢአት ይጠመዳል፤ጻድቅ ግን ይዘምራል፤ ደስም ይለዋል።
7. ጻድቅ ለድኾች ፍትሕ ይጨነቃል፤ክፉ ሰው ግን ደንታ የለውም።
8. ተሳዳቢዎች ከተማን ያውካሉ፤ጠቢባን ግን ቊጣን ያበርዳሉ።
9. ጠቢብ ሰው ከተላላ ጋር ወደ ሸንጎ ቢሄድ፣ተላላ ይቈጣል፤ ያፌዛል፤ ሰላምም አይኖርም።
10. ደም የተጠሙ ሰዎች ሐቀኛን ሰው ይጠላሉ፤ቅን የሆነውንም ለመግደል ይሻሉ።
11. ተላላ ሰው ቊጣውን ያለ ገደብ ይለቀዋል፤ጠቢብ ሰው ግን ራሱን ይቈጣጠራል።
12. ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።
13. ድኻውና ጨቋኙ የጋራ ነገር አላቸው፤ እግዚአብሔር ለሁለቱም የዐይን ብርሃንን ሰጥቶአቸዋል።
14. ንጉሥ ለድኻ ትክክለኛ ፍርድ ቢሰጥ፣ዙፋኑ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
15. የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።