ምሳሌ 29:3-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ጥበብን የሚወድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤የአመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል።

4. ፍትሕን በማስፈን ንጉሥ አገርን ያረጋጋል፤ጒቦ ለማግኘት የሚጐመጅ ግን ያፈራርሳታል።

5. ባልንጀራውን የሚሸነግል፣ለገዛ እግሩ መረብ ይዘረጋል።

6. ክፉ ሰው በራሱ ኀጢአት ይጠመዳል፤ጻድቅ ግን ይዘምራል፤ ደስም ይለዋል።

7. ጻድቅ ለድኾች ፍትሕ ይጨነቃል፤ክፉ ሰው ግን ደንታ የለውም።

8. ተሳዳቢዎች ከተማን ያውካሉ፤ጠቢባን ግን ቊጣን ያበርዳሉ።

9. ጠቢብ ሰው ከተላላ ጋር ወደ ሸንጎ ቢሄድ፣ተላላ ይቈጣል፤ ያፌዛል፤ ሰላምም አይኖርም።

10. ደም የተጠሙ ሰዎች ሐቀኛን ሰው ይጠላሉ፤ቅን የሆነውንም ለመግደል ይሻሉ።

ምሳሌ 29