ምሳሌ 28:25-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ስስታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል።

26. በራሱ የሚታመን ተላላ ነው፤በጥበብ የሚመላለስ ግን ክፉ አያገኘውም።

27. ለድኾች የሚሰጥ አይቸገርም፤አይቶአቸው እንዳላየ የሚሆን ግን ብዙ ርግማን ይደርስበታል።

ምሳሌ 28