ምሳሌ 27:4-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ንዴት ጨካኝ፣ ቊጣም ጐርፍ ነው፤በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?

5. የተገለጠ ዘለፋ፣ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።

6. ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣የወዳጅ ማቊሰል ይታመናል።

7. ለጠገበ ማር አይጥመውም፤ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል።

8. ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ጎጆዋን ለቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው።

9. ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል።

10. የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።

11. ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሰኘው፤ለሚንቁኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችል ዘንድ።

12. ጥንቁቅ አደጋን አይቶ ይሸሸጋል፤ማስተዋል የጐደለው ግን ወደዚያው ይሄዳል፤ ይጐዳልም።

ምሳሌ 27