ምሳሌ 27:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ሌላው ያመስግንህ እንጂ የገዛ አፍህ አይደለም፤ሌላ ሰው ያወድስህ እንጂ የገዛ ከንፈርህ አይሁን።

3. ድንጋይ ይከብዳል፤ አሸዋም ሸክም ነው፤የተላላ ሰው ጒነጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።

4. ንዴት ጨካኝ፣ ቊጣም ጐርፍ ነው፤በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?

5. የተገለጠ ዘለፋ፣ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።

ምሳሌ 27