ምሳሌ 26:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ሁሉ፣ተላላም ቂልነቱን ይደጋግማል።

12. ራሱን እንደ ጠቢብ የሚቈጥረውን ሰው አይተሃልን?ከእርሱ ይልቅ ለተላላ ተስፋ አለው።

13. ሰነፍ፣ “በመንገድ ላይ አንበሳ አለ፤አስፈሪ አንበሳ በአውራ ጐዳና ላይ ይጐማለላል” ይላል።

14. መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ሰነፍም በዐልጋው ላይ ይገላበጣል።

ምሳሌ 26