ምሳሌ 25:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ክፉን ከንጉሥ ፊት አርቅ፤ዙፋኑም በጽድቅ ትጸናለች።

6. በንጉሥ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤በታላላቆች መካከል መገኘትም አይመርህ፤

7. በትልቅ ሰው ፊት ከሚያዋርድህ፣ራሱ፣ “ወደዚህ ከፍ በል” ቢልህ ይሻላልና።በዐይንህ ያየኸውን ሁሉ፣

8. ወደ ፍርድ አደባባይ በችኰላ አታውጣው፤ባልንጀራህ ካሳፈረህ፣ኋላ ምን ይውጥሃል?

9. ስለ ራስህ ጒዳይ ከባልንጀራህ ጋር በምትከራከርበት ጊዜ፣የሌላውን ሰው ምስጢር አታውጣ፤

ምሳሌ 25