ምሳሌ 25:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ባግባቡ የተነገረ ቃል፣በብር መደብ ላይ እንደ ተቀረጸ የወርቅ እንኮይ ነው።

12. የጠቢብ ሰው ዘለፋ ለሚሰማ ጆሮ፣እንደ ወርቅ ጒትቻ ወይም እንደ ጥሩ የወርቅ ጌጥ ነው።

13. በመከር ጊዜ የበረዶ ቅዝቃዜ ለሰስ እንደሚያደርግ ሁሉ፣ታማኝ መልእክተኛም ለላኩት እንደዚሁ ነው፤የጌቶቹን መንፈስ ያሳርፋልና።

14. የማይለግሰውን ስጦታ እቸራለሁ ብሎ ጒራ የሚነዛ ሰው፣ዝናብ እንደሌለው ደመናና ነፋስ ነው።

ምሳሌ 25