ምሳሌ 23:5-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. በሀብት ላይ ዐይንህን ብትጥል፤ወዲያው ይጠፋል፤ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር፣ በርግጥ ክንፍ አውጥቶ ይበራል፤

6. የስስታምን ምግብ አትብላ፤ጣፋጭ መብሉም አያስጐምጅህ፤

7. ሁል ጊዜ ስለ ዋጋ የሚያሰላ ሰው ነውና፤“ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም።

8. የበላሃት ትንሿ እንኳ ታስመልስሃለች፤የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ።

9. ከጅል ጋር አትነጋገር፤የቃልህን ጥበብ ያንኳስሳልና።

10. የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ፤አባት የሌላቸውንም ልጆች መሬት አትግፋ፤

11. ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፤እርሱ ይፋረድላቸዋል።

12. ልብህን ለምክር፣ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል ስጥ።

ምሳሌ 23