ምሳሌ 23:22-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. የወለደህን አባትህን አድምጥ፤እናትህንም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።

23. እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት፤ጥበብን፣ ተግሣጽንና ማስተዋልን ገንዘብህ አድርግ።

24. የጻድቅ ሰው አባት እጅግ ደስ ይለዋል፤ጠቢብ ልጅ ያለውም በእርሱ ሐሤት ያደርጋል።

25. አባት እናትህ ደስ ይበላቸው፤ወላጅ እናትህም ሐሤት ታድርግ።

26. ልጄ ሆይ፤ ልብህን ስጠኝ፤ዐይኖችህም ከመንገዴ አይውጡ፤

ምሳሌ 23