ምሳሌ 22:22-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤

23. እግዚአብሔር ይፋረድላቸዋልና፤የሚቀሟቸውንም ይቀማቸዋል።

24. ከግልፍተኛ ጋር ወዳጅ አትሁን፤በቀላሉ ቱግ ከሚልም ሰው ጋር አትወዳጅ፤

25. አለበለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤ራስህም ትጠመድበታለህ።

26. በዋስትና ቃል እጅ አትምታ፤ለብድር ተያዥ አትሁን፤

ምሳሌ 22