ምሳሌ 21:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. የበደለኛ መንገድ ጠማማ ነው፤የንጹሕ ሰው ጠባይ ግን ቀና ነው።

9. ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር፣በጣራ ላይ ጥግ ይዞ መኖር ይሻላል።

10. ክፉ ሰው ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤ባልንጀራውም ከእርሱ ዘንድ ርኅራኄን አያገኝም።

11. ፌዘኛ ሲቀጣ፣ አላዋቂ ጥበብን ያተርፋል፤ጠቢብ ሰው ቢማር ዕውቀትን ያገኛል።

12. ጻድቁ የክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል።

ምሳሌ 21