ምሳሌ 21:16-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

17. ቅንጦትን የሚወድ ይደኸያል፤የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድም ባለጠጋ አይሆንም።

18. ክፉ ሰው ለጻድቅ፣ወስላታም ለቅን ሰው ወጆ ይሆናል።

19. ከጨቅጫቃና ከቊጡ ሚስት ጋር ከመኖር፣በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።

20. በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤ተላላ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።

21. ጽድቅንና ፍቅርን የሚከተል፤ሕይወትን ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።

22. ጠቢብ የኀያላንን ከተማ ቅጥር ጥሶ ይገባል፤መታመኛ ምሽጋቸውንም ያፈርሳል።

23. አንደበቱንና ምላሱን የሚቈጣጠር፣ራሱን ከመቅሠፍት ይጠብቃል።

24. ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው፣ ኋፌዘኛቃ ይባላል፤በጠባዩም እብሪተኛ ነው።

25. ታካችን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።

26. ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል።

27. የክፉ ሰው መሥዋዕት አጸያፊ ነው፤በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን!

28. ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤እውነቱን የሚናገር ግን ጸንቶ ይኖራል።

29. ክፉ ሰው በዐጒል ድፍረት ይቀርባል፤ቅን ሰው ግን አደራረጉን ያስተውላል።

30. እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣አንዳችም ጥበብ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።

ምሳሌ 21