ምሳሌ 21:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

17. ቅንጦትን የሚወድ ይደኸያል፤የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድም ባለጠጋ አይሆንም።

18. ክፉ ሰው ለጻድቅ፣ወስላታም ለቅን ሰው ወጆ ይሆናል።

ምሳሌ 21