ምሳሌ 20:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ሰነፍ ሰው በወቅቱ አያርስም፤ስለዚህ በመከር ወራት ይፈልጋል፤አንዳችም አያገኝም።

5. የሰው ልብ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤አስተዋይ ሰው ግን ከዚያ ቀድቶ ያወጣዋል።

6. ብዙ ሰው ጽኑ ፍቅር እንዳለው ይናገራል፤ታማኝን ሰው ግን ማን ሊያገኘው ይችላል?

7. ጻድቅ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት ይመራል፤ከእርሱም በኋላ የሚከተሉት ልጆቹ ቡሩካን ናቸው።

8. ንጉሥ ለፍርድ ዙፋኑ ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ አበጥሮ ይለያል።

ምሳሌ 20