ምሳሌ 20:24-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር ይመራል፤ሰውስ የገዛ መንገዱን እንዴት ማስተዋል ይችላል?

25. በችኰላ ስእለት መሳል፣ከተሳሉም በኋላ ማቅማማት ለሰው ወጥመድ ነው።

26. ጠቢብ ንጉሥ ክፉዎችን አበጥሮ ይለያል፤የመውቂያ መንኰራኵርንም በላያቸው ላይ ይነዳል።

27. የሰው መንፈስ ለእግዚአብሔር መብራት ነው፤ውስጣዊ ማንነቱንም ይፈትሻል።

28. ፍቅርና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤በፍቅርም ዙፋኑ ይጸናል።

29. የጎልማሶች ክብር ብርታታቸው፣የሽማግሌዎችም ሞገስ ሽበታቸው ነው።

ምሳሌ 20