ምሳሌ 20:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤በእነዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም።

2. የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤የሚያስቈጣውም ሰው ሕይወቱን ለመከራ ይዳርጋል።

3. ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤ተላላ ሁሉ ግን ለጥል ይቸኵላል።

ምሳሌ 20