ምሳሌ 2:5-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. በዚያን ጊዜ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ትረዳለህ፤አምላክንም ማወቅ ታገኛለህ።

6. እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ከአንደበቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣል።

7. እርሱ ለቅኖች ድልን ያከማቻል፤ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ይሆናቸዋል፤

8. የፍትሕን መንገድ ይጠብቃል፤የታማኞቹንም አካሄድ ያጸናል።

9. በዚያን ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትሕን፣ ሚዛናዊነትን፣መልካሙንም መንገድ ሁሉ ትገነዘባለህ፤

10. ጥበብ ልብህ ውስጥ ትገባለችና፤ዕውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፤

ምሳሌ 2