ምሳሌ 2:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ጥበብ ንግግራቸው ጠማማ ከሆነ ሰዎች፣ከክፉዎችም መንገድ ታድንሃለች፤

13. እነዚህም በጨለማ መንገድ ለመሄድ፣ቀናውን ጐዳና የሚተዉ ናቸው፤

14. ክፉ በመሥራት ደስ የሚላቸው፣በክፋት ጐዳና ሐሤት የሚያደርጉ፣

15. መንገዳቸው ጠማማ፣በአካሄዳቸው ጠመዝማዞች ናቸው።

16. ከአመንዝራ ሴትም ትጠብቅሃለች፤በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ታድንሃለች፤

ምሳሌ 2