4. ሀብት ብዙ ወዳጅ ታፈራለች፤ድኻን ግን ወዳጁ ገሸሽ ያደርገዋል።
5. ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ውሸት የሚነዛም ሳይቀጣ አይቀርም።
6. ብዙ ሰዎች በገዥ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያሸረግዳሉ፤ስጦታን ከሚሰጥ ሰው ጋር ሁሉም ወዳጅ ነው።
7. ድኻ በሥጋ ዘመዶቹ ሁሉ የተጠላ ነው፤ታዲያ ወዳጆቹማ የቱን ያህል ይሸሹት!እየተከታተለ ቢለማመጣቸውም፣ከቶ አያገኛቸውም።
8. ጥበብን ገንዘቡ የሚያደርጋት ነፍሱን ይወዳል፤ማስተዋልን የሚወዳት ይሳካለታል።
9. ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ውሸት የሚነዛም ይጠፋል።