15. ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ዋልጌም ሰው ይራባል።
16. ትእዛዛትን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፤መንገዱን የሚንቅ ግን ይሞታል።
17. ለድኻ የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ስላደረገውም ተግባር ዋጋ ይከፍለዋል።
18. ገና ተስፋ ሳለ፣ ልጅህን ሥርዐት አስይዘው፤ሲሞት ዝም ብለህ አትየው።
19. ግልፍተኛ ሰው ቅጣትን መቀበል ይገባዋል፤በምሕረት ካለፍኸው ሌላም ጊዜ አይቀርልህም።
20. ምክርን ስማ፤ ተግሣጽን ተቀበል፤በመጨረሻም ጠቢብ ትሆናለህ።
21. በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው።
22. ሰው የሚመኘው ጽኑ ፍቅር ነው፤ውሸታም ከመሆንም ድኻ መሆን ይሻላል።
23. እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤እንዲህ ያለውም ሰው እፎይ ብሎ ያርፋል፤ መከራም አያገኘውም።
24. ሰነፍ እጁን ከወጭቱ ያጠልቃል፤ወደ አፉ ግን መመለስ እንኳ ይሳነዋል።
25. ፌዘኛን ግረፈው፤ ብስለት የሌለውም ማስተዋልን ይማራል፤አስተዋይን ዝለፈው፤ ዕውቀትን ይገበያል።
26. አባቱን የሚዘርፍ፣ እናቱንም የሚያሳድድ፣ዕፍረትና ውርደት የሚያመጣ ልጅ ነው።
27. ልጄ ሆይ፤ እስቲ፣ ምክርን ማዳመጥ ተው፤ከዕውቀትም ቃል ትስታለህ።
28. ዐባይ ምስክር በፍትሕ ላይ ያፌዛል፤የክፉዎችም አፍ በደልን ይሰለቅጣል።