ምሳሌ 19:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ንግግሩ ጠማማ ከሆነ ዐጒል ሰው ይልቅ፣ያለ ነውር የሚሄድ ድኻ ሰው ይሻላል።

2. ዕውቀት አልባ የሆነ ቀናዒነት መልካም አይደለም፤ጥድፊያም መንገድን ያስታል።

3. ሰው በራሱ ተላላነት ሕይወቱን ያበላሻል፤በልቡ ግን እግዚአብሔርን ያማርራል።

4. ሀብት ብዙ ወዳጅ ታፈራለች፤ድኻን ግን ወዳጁ ገሸሽ ያደርገዋል።

5. ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ውሸት የሚነዛም ሳይቀጣ አይቀርም።

ምሳሌ 19