ምሳሌ 18:20-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ሰው በአንደበቱ ፍሬ ሆዱ ይጠግባል፤በከንፈሩም ምርት ይረካል።

21. አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤የሚወዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።

22. ሚስት የሚያገኝ መልካም ነገርን ያገኛል፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል።

23. ድኻ በመለማመጥ ምሕረት ይለምናል፤ሀብታም ግን በማናለብኝነት ይመልሳል።

ምሳሌ 18