ምሳሌ 17:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልስ ሰው፣ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።

14. ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።

15. በደለኛውን ንጹሕ ማድረግ ሆነ፣ ንጹሑን በደለኛ ማድረግ፣ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ናቸው።

ምሳሌ 17