ምሳሌ 17:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. መቶ ግርፋት ተላላን ከሚሰማው ይልቅ፣ተግሣጽ ለአስተዋይ ጠልቆ ይሰማል።

11. ክፉ ሰው ዐመፅን ብቻ ይፈልጋል፤በእርሱም ላይ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።

12. ተላላን በቂልነቱ ከመገናኘት፣ግልገሎቿን የተነጠቀችን ድብ መጋፈጥ ይሻላል።

13. በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልስ ሰው፣ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።

14. ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።

ምሳሌ 17